የአብክመ አመራር አካዳሚ ሰራተኞች ዓለም አቀፍ የሴቶችን ቀን አከበሩ

የአብክመ አመራር አካዳሚ አመራሮችና ሰራተኞች “እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ” በሚል መሪ ቃል አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በዓል በደማቅ ሁኔታ አከበሩ ።በዓሉ ሲከበር የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአካዳሚዉ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ እና ተወካይ የአስ/ልማ/ም/ኃላፊ አቶ ምህረቴ ዋለ በአለም አቀፍ ለ111ኛ ጊዜ በአገራችን ለ46ኛ ጊዜ” እኔ ለእህቴ ጠባቂ ነኝ” በሚል መሪ ቃል ለሚከበረው የሴቶች ቀን እንኳን አደረሳችሁ ብለው የበዓሉ መከበር የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ፤ፖለቲካዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት እንዲሁም የፆታ እኩልነትን ለማረጋገጥ በተደረገዉ ትግል የሴቶችን የማይተካ ተሳትፎ ለመዘከርና በለዉጡ ሂደት ዉስጥ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና አጋርነትን የበለጠ ማጠናከር ለሀገራችን ሠላም ወሳኝ ነው በማለት ገልፀዋል፡፡

የአካዳሚዉ የስርዓተ-ፆታ እና ኤች አይ ቪ/ኤድስ ባለሙያ በሆኑት ወ/ሮ ያለም መብራት ዋለ የመወያያ ጽሁፍ የቀረበ ሲሆን በጽሁፋቸው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ታሪካዊ አመጣጥ እና በሰላምና ተያያዥ ጉዳዮች አካተው የውይይት መነሻ አቅርበዋል፡፡ወ/ሮ ያለም መብራት በጹሁፋቸው ሴቶች ከማንም እንደማያንሱና እንዲያውም የተሸለ ሀላፊነትን በመሸከምና በብቃት የመወጣት ብቃት ያላቸው መሆኑን በጹፋቸው ጠቅሰዋል፡፡አቅራቢዋ አክለውም ሰላን እንደ ግለሰብ፤እንደ ተቋም እና እንደ ሀገር ለማምጣት የህግ የበላይነትን ማክበር፤ይቅርታ ማድረግና መቀበል እንዲሁም የትውልድ ለትውልድ ግንኙነቶችን ማስተካከል ይገባና በማለት ገልፀዋል፡፡የአካዳሚዉ በምክትል ቢሮ ሀላፊ ደረጃ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆኑት አቶ ጋሻው ገብሬ ውይይቱን ሲያጠቃልሉ በበኩላቸዉ ያለሴቶች ተሳትፎና አጋርነት ለዉጥ ሊመጣ አይችልም፤ ሴቶች ከወንዶች የተሻለ የመምራት አቅም፤ ታማኝነት፤ አዳዲስ ሃሳቦችን የማፍለቅ አቅም ያላቸዉ በመሆኑ ለዉጥና እድገት ከተፈለገ ሴቶች ወደ ፊት ሊመጡ ይገባል ብለዋል፡፡በመጨረሻም በሀገር አቀፍ በነበረው የህልውና ዘመቻ ተሳታፊ ለነበሩት ጀግኒት ያለምዘውድ አድማሱና ጀግናው ሻረው ይግዛው እውቅና በመስጠት የዕለቱን ውይይት አጠቃለዋል፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *