የአማራ አመራር አካዳሚ የምኝታ አገልግሎት(Bed service )

አገልግሎቱን ፈልገው ለሚመጡ ተቋማትና ሠልጣኞች በአንድ ጊዜ 300 ሰልጣኞችን ማስተናገድ የሚችሉ ንፁህ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ አልጋዎች አሉን፡፡ ደረጃ አንድ አልጋ ክፍሎች ውስጥ የውስጥ ሻውርና ሽንት ቤት፣ ሳሎን ክፍል ሶፋ፣ሸልፍ ቲቪ ፍሪጅ ፎጣ፣ የፅዳት መጠበቂያ ቁሳቁሶች ንፁህ አልባሳት ይኖሩታል፤ ደረጃ ሁለት አልጋ ክፍል የውስጥ ሻውርና ሽንት ቤት፣ ሸልፍ፣ ፎጣ፣ የጽዳት መጠበቂያ ቁሳቁስ፣ ንፁህ አልባሳት ይኖሩታል፡፡

ደረጃ ሦስት አልጋ ክፍል ሸልፍ፣ የፅዳት መጠበቂያ ቁሳቁስ ፎጣ፣ ንፁህ አልባሳት፣ ሁለት አልጋዎች በአንድ ክፍል፣/double bed/ እና የጋራ መጠቀሚያ ሽንት ቤት ይኖረዋል፡፡