ለ2ኛና ለ3ኛ ዲግሪ የቅበላ መስፈርቶች
1. ለ2ኛ ዲግሪ
1.1 እድሜ፤ እስከ 50 ዓመት እድሜ ያላቸው ለውድድር የሚቀርቡ ይሆናሉ፡፡
1.2 የትም/ ደረጃ ና ዝግጅት 20 % ሆኖ እውቅና በተሰጣቸው የትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቀ ሁኖ(ና) ጂፒኤ የተወዳደሪዎች ነጥብ ≥ 2.00 ሆኖ እያንዳንዱ ነጥብ በ5 እንዲባዛ ይደረጋል፡፡
1.3 የጹሁፍ መግቢያ ፈተና (75%) ሆኖ ፈተናው እውቀት፤ክህሎትና አመለካከትን በተገቢው ሁኔታ የሚለካ ጥያቄዎች ይዘጋጃል፡፡
1.4 የስራ ልምድ (Work Experience) 5% ሆኖ የስራ ልምድ ነጥብ አያያዝ ከ≥5 ዓመት በላይ ልምድ ያለቸው ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ የአመራርነት ልምድ ያላቸው 5%) የሚሰጥ ሁኖ ሌሎቹ እንደየስራ ልምዳቸው ነጥብ ይያዛል፡፡
2 .1 ለ3ኛ ዲግሪ
2.2 እድሜ (5%) የሚይዝ ሆኖ እስከ 50 ዓመት እድሜ ያላቸው ለውድድር የሚቀርቡ ይሆናሉ፡፡ የነጥብ አሰጣጡም እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
- ≤ 45 እድሜ ነጥብ (5%)
- 46 እድሜ ነጥብ (4%)
- 47 እድሜ ነጥብ (3%)
- 48 እድሜ ነጥብ (2%)
- 49 እድሜ ነጥብ (1%)
- 50 እድሜ ነጥብ (0%)
2.3 የ2ኛ ዲግሪ ትምህርት ውጤት ≥ 3.0 ነጥብ (10%) የሚይዝ ሆኖ እያንዳንዱ ነጥብ በ2.50 ይባዛል፡፡
2.4 የ2ኛ ዲግሪ የመመረቂያ ጹሁፍ (5%) የሚይዝ ሆኖ ውጤት B እና በላይ ወይም Good እና በላይ መሆን አለበት፡፡
- Good የተሰጠ ነጥብ (3%)
- Very Good የተሰጠ ነጥብ (4%)
- Excellent የተሰጠ ነጥብ (5%)
2.5 የጹሁፍ መግቢያ ፈተና (45%) ፈተናው እውቀት፤ክህሎትና አመለካከት በተገቢው ሁኔታ የሚለካ ጥያቄዎች ይዘጋጃል፡፡
2.6 አጭር የምርምር ንድፈ ሃሳብ (Synopsis) ማቅረብ (30%) ሆኖ ከ2ገጽ ባልበለጠ የምርምር መነሻ ሃሳብ፤ ጥቅል አላማና ሊከተል የሚገባውን ዘዴ ያካተተ ጹሁፍ በማቅረብ መቋቋም (defened) ማድረግ አለባቸው፡፡
2.7 የስራ ልምድ (Work Experience) (5%)
- በአካዳሚው ገብተው የመደበኛ ትምህርት የሚማሩ በስራ ላይ ያሉ አመራሮችና ባለሙያዎች በመሆናቸው ከሚሰሩበት ተቋም አግባብነት ያለው የስራ ልምድ የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የስራ ልምድ ነጥብ አያያዝ ከ≥ 20ዓመት የሆናቸው (5%) የሚሰጥ ከ20 ዓመት በታች ያሉ የስራ ልምዶች በ0.25 በማባዛት ይሰላል፡፡
- ለምዝገባ የሚያስፈልጉ መረጃዎች
- የመጀመሪያና 2ኛ ዲግሪ የትም/ውጤት ኦሪጅናል እንዲሁም ከተመረጡ በኋላ (Official Transcript) ከተማሩበት ተቋም ለአካዳሚው (በፖ.ሳ.ቁ. 1217 አመራር አካዳሚ) ማስላክ አለባቸው፡፡
- የስራ ልምድ ማስረጃ፤
- በ2ኛና 3ኛ ዲግሪ ለሚወዳደሩ ተወዳደሪዎች በመንግስት ስፖንሰር እንዲማሩ ከተፈቀደላቸው ውጪ የወጪ መጋራት (Cost sharing) ነጻ መሆናቸውን የሚያጋግጥ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተወዳደሪዎች ከሚሰሩበት ተቋም የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተቋሙ የሚሸፍናቸውና የማይሸፍናቸው ጉዳዩች
- አካዳሚው የምኝታ አገልግሎት ብቻ የሚሰጥ ሲሆን ለመማር የተመረጡ ተወዳዳሪዎች ብርድልብስ፣አንሶላና የትራስ ልብስ ይዘው መምጣት ይጠበቅባቸዋል
- አካዳሚው የምግብ አገልግሎት አይሰጥም፡፡
- በአካዳሚው የሚማሩ ተማሪዎች በመንግስት የተላኩ አመራሮችና ባለሙያዎች ከሆኑ የትምህርት ወጪአቸው በክልሉ ሲቪል ሰርቪስ በኩል በጀት እንዲያዝ የሚደረግ ሲሆን ከሌሎች ተቋማት (ከልማት ድርጅቶች፤ከሃይማኖት ተቋማት፤ በግል ድርጅቶች) ለሚመጡ ግን ሙሉ ወጪያቸው የሚሸፈነው በራሳቸው ተቋም ወይም ድርጅት ይሆናል፡፡
- ልዩ ሁኔታ
5.1. የ2ኛና 3ኛ ዲግሪ ሴት ተወዳደሪዎች በውድድሩ የሚበረታቱ ሲሆን ካገኙት (100%) በልዩ ሁኔታ (5%) ለሴቶች ይሰጣል፡፡
- የፈተና ጊዜ፤- ወደፊት በማስታወቂያና በተቋሙ ድህረ-ገጽ የሚገለጽ ይሆናል ፡፡
ከዚህ በላይ 1.1 ፣ 1.2 ፣ 1.4፣ 2.1 ፣2.2 ፣ 2.3 እና 2.6 የተገለጹት ማለትም ( የትም/ውጤት (CGPA)፣የመመረቂያ ጹሁፍ፤ ዕድሜና የስራ ልምድ ) የተጠቀሱት ነጥቦች እንደተጠበቁ ሆነው ተቋማት ሌሎችን የማወዳደሪያ መስፈርት በራሳችሁ መጠቀም ይችላሉ፤
- ተወዳዳሪዎች በተቋማቸው ከተመለመሉበት ጊዜ ጀምሮ በአካዳሚው ለሚሰጠው ፈተና ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ሆኖ በአካዳሚው ለመግቢያ ፈተና የተመረጡ ተወዳዳሪዎች (SELECTED) በድህረ ገጻችን የምናሳውቅ ይሆናል፡፡
- ተመዝጋቢዎች የትምህርት ማስረጃዎች ከዋናው ጋር የተገናዘበ ኮፒ በአወዳዳሪው መ/ቤት በኩል ለአካዳሚው መቅረብ አለበት፡፡
- ለ3ኛ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርት የሚጀመረው በ1ኛው ወሰነ ትምህርት ሲሆን
- ለ2ኛ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርት የሚጀመረው በ2ኛው ወሰነ ትምህርት መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስ.ቁ 0583209891 /0918707648/0918023551 መደወል ይቻላል፡፡