የአማራ አመራር አካዳሚ ለሳይንስና ቴክኖሎጅ፤ኢንፎርሜሸን ኮሙዩኒኬሽን ኮሚሽን ሰራተኞች የካይዘን ስራ አመራር ስልጠና ሰጠ

የአማራ አመራር አካዳሚ ለሳይንስና ቴክኖሎጅ፤ኢንፎርሜሸን ኮሙዩኒኬሽን ኮሚሽን ሰራተኞች ከመጋቢት 06/2013 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት በከይዘን ስራ አመራር ፍልስፍና አተገባበር ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል፡፡ስልጠናዉ በአካዳሚዉ የስራ አመራር ልማት ዳይሬክተር አቶ ዮሐንስ ወርቁ እና በአካዳሚዉ  አማካሪዎች በጋራ እየተሰጠ ይገኛል፡፡የከይዘን የስራ አመራር ፍልስፍናን በተገቢዉ በመተግበር ብክነትና ወጭን በመቀነስ ምርታማነትንና ጥራትን በማሳደግ ቀልጣፋና ዉጤታማ የሆነ አገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን በማስፈን ለዉጥና መሻሻልን በዘለቄታዊነት ለማስቀጠል ተቋማት የህዝብ አገልጋይነት መንፈስ እንዲላበሱ ማድረግ መሆኑ ስልጠና ተመላክቷል፡፡

አመራር አካዳሚዉ የከይዘን ስራ አመራር ፍልስፍናን በክልሉ ባሉ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ለማስረፅ በስልጠና በምክርና ስርፀት አገልግሎት በመስጠት ሰፊ ንቅናቄ እያደረገ ይገኛል፡፡ አመራር አካዳሚዉ በሁሉም መንግስታዊና የልማት ድርጅቶች ከይዘናዊ የስራ ባህል ትራንስፎርሜሽን በማምጣት በክልላችን የሚስተዋለዉን የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች ማሻሻልና የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ጠንክሮ መስራትና የክልላችን ሞዴል የልህቀት ማዕከል በመሆን የከይዘን ስራ አመራር ፍልስፍናን ወደ ማያቋርጥ የለዉጥ ደረጃ ለማድረስ በትኩረት እየሰራ ነዉ ፡፡ በዚህም መሰረት የሳይንስና ቴክኖሎጅ፤ኢንፎርሜሸን ኮሙዩኒኬሽን ኮሚሽን ሰራተኞች በስልጠናዉ እንዲሳተፉ በማድረግ  የተቋሙን  ተልዕኮ ዕቅድ ከማሳካት አኳያ ዉጤታማ ለማድረግ የሰውና  የቁሳዊ ሀብትንና ጊዜን በተቀናጀና በውጤታማ መልኩ ለመጠቀም እንዲችሉ  በተገቢዉ አሰልጥኗል፡፡

አካዳሚዉ የከይዘን ስራ አመራር ፍልስፍናን በክልላችን ዉጤታማ ለማድረግና ለማስረፅ ክልላዊ ኃላፊነት ወስዶ እየሰራ እንደሚገኝ ይታወሳል፡፡በስልጠናዉ ከ48 በላይ የዞን እና የክልሉ  ሳይንስና ቴክኖሎጅ፤ኢንፎርሜሸን ኮሙዩኒኬሽን ኮሚሽን ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡