የአማራ አመራር አካዳሚ የ2013 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት አፈፃፀም ግምገማዊ ዉይይት አካሄደ
የካቲት 22/06/2013 ዓ.ም የአማራ አመራር አካዳሚ ሰራተኞች በ2013 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ዕቅድ ክንዉን አፈፃፀም ግምገማዊ የውይይት መድረክ አካሂደዋል፡፡
የአካዳሚው ዕቅድ፤በጀትና ፕሮጀክት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት አቶ ያረጋል ዳምጤ በግማሽ አመቱ በእቅድ ከተያዙት የቁልፍና አበይት ተግባራት ዉስጥ አብዛኞቹ ተግባራት በተሻለ ሁኔታ ማከናወን መቻሉን ባቀረቡት ሪፖርት አመላክተዋል፡፡ አቶ ያረጋል አክለውም ባለፉት ስድስት ወራት ሁሉንም የቁልፍና አበይት ስራዎችን ከእቅዱ ጋር በተጣጣመ መልኩ መፈፀሙ፤ስራዎችን በስታንዳርድ መሰረት መፈፀም፤ የተሳካ የመማር ማስተማር ሥራ፤ መደበኛና አጫጭር ልዩ ልዩ ስልጠናዎች፤ የነባሩ ህንፃ ርክክብ፤ የአሰራርና አደረጃጀት ስራዎች መሻሻል፤ የተቀረፁ የገቢ ማስገኛ ፕሮጀክቶች፤ የሰራተኛዉ አገልግሎት አሰጣጥ መሻሻልና ቅንጅታዊና ቡድናዊ አሰራሮች መጎልበት በጥንካሬ ጠቅሰዋል፡፡ በውይይቱ ተሳታፊ ሰራተኞችም የከይዘን ስራ አመራር ፤የህንፃ ግንባታዎችና የነባሩ ህንፃ ጥገና፤ የፕሮጀክት ቀረፃ ስራዎች፤የሰራተኛዉ የአቅም ግንባታ ስራዎች ማደግ ያለባቸዉ መሆኑን አስተያየቶችና በርካታ ጥያቄዎች ተነስተው በአካዳሚዉ የበላይ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
በመጨረሻም የአብክመ አመራር አካዳሚ ፕሬዘዳንት የሆኑት ዶ/ር ማተቤ ታፈረ ውይይቱን በመሩበት ወቅት እንደተናገሩት በቀጣይ ጊዜአት ለክልላችን ብሎም ለሀገራችን አለኝታ የሚሆን ተቋም ለመገንባት ሁላችንም ወጥ በሆነ መልኩ በትጋት መፈፀምና በተነሳሽነት ማከናወን ይገባል በማለት አሳስበዋል፡፡ ደ/ር ማተቤ አያይዘውም አካዳሚያቸን በዚህ ግማሽ ዓመት ላከናወናቸው ተሻሉና እና መልካም ውጤቶች እንዲሁም የክልሉ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ለመሆን ለምናደርገው ጉዞ መሳካት እና እዚህ ደረጃ መድረስ የሁሉም ሰራተኞች ርብርብ በመሆኑ በማመስገን እና በቀጣይ ቀን የስሜት ብልህነት በሚል ርዕስ ለሁሉም ሰራተኞች ስልጠና እንደሚሰጥ በማሳወቅ የእቅድ አፈፃፀሙን ውይይት ዘግተዋል፡፡