ቀን :-16/07/2014 ዓ.ም
የአማራ ክልል አመራር አካዳሚ ከገጠር ልማት ስትራቴጅና ሞዴል መንደር ምስረታ ማማከር ኘሮጀክት ጋር በመተባበር በክልሉ ዉሥጥ ከሚገኙ አራት ወረዳዎች የተመረጡ 80 የመንደር አመራሮችን ከመጋቢት 12 እስከ መጋቢት 14 ቀን 2014 ዓ.ም ለአምስት ተከታታይ ቀናት በአካዳሚዉ ግቢ የስልጠና አዳራሽ ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና አጠናቀቀ፡፡
በስልጠናው ማጠቃለያ ፕሮግራም የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በምክትል ቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአካዳሚዉ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጋሻዉ ገብሬ እንደገለፁት አገር የምትመሰረተዉ ሰዉ ራሱን በቤት በመንደርና በአካባቢ መለወጥና ማበልፀግ እንዲሁም ለሌሎች አርአያ መሆን ሲቻል መሆኑን ገልፀዉ፤የተቀናጀ የገጠር ልማት ፕሮጀክትን በዉጤት በመተግበር የእያንዳንዱን ግለሰብ ህይወት መለወጥ እንዲችል በመሆኑ ከስልጠናዉ ያገኛችሁትን እዉቀትና ክህሎት ወደ ተግባር መቀየር ይገባል ብለዋል፡፡
ለተከታታይ አምስት ቀናት የተሰጠው ስልጠና የደቡብ ኮሪያን ፈጣን የገጠር ልማት ዕድገት ከአማራ ክልል ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማጣጣም የክልሉን የገጠር መንደሮች በአጭር ጊዜ እንዲለሙ እና ለአገር እድገት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ የሞዴል አርሶ አደሮችን አቅም መገንባት የሚያስችል ስልጠና መሆኑም ተመላክቷል፡፡
ስልጠናው በዋናነት የገጠር አመራር ጥበብ፤የእቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ፤የህዝብ ተሳትፎ፤የስራ ባህል ግንባታና የአመራሩ ሚና እና የደቡብ ኮሪያ አዲስ መንደር ንቅናቄ ተሞክሮ ላይ ያተኮሩ የስልጠና ርዕሶች ተለይተዉ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
በክብር እንግድነት ተገኝተዉ የስራ መመሪያ የሰጡት የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አልማዝ ጊዜዉ(ዶ/ር) በበኩላቸዉ መሪ ብርሀን ፈንጣቂ፤ንቁ፤አዋቂ፤ትጉህና ጀግና ሆኖ ሌሎችን የሚያጀግን መሆን አለበት፤የስልጠናዉ ዓላማም መንደር ተለዉጦ ሀገር እንዲለወጥ ንቁና ጤናማ ማህበረሰብ በመገንባት ዘመናዊ የግብርና ትራንስፎርሜሽን በማምጣት የምግብ ዋስትናችንን ማረጋገጥ ይኖርብናል ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ለስልጠና ተሳታፊ ሞዴል አርሶ አደሮች የእዉቅናና ሰርተፊኬት ስነ-ስርዓት ተበርክቶላቸዋል፡፡ በቀጣይም የዚህ አይነት ስልጠና በአካዳሚዉና በፕሮጅክቱ ትብብር በየደረጃዉ ለሚገኙ የቀበሌና የወረዳ አመራሮች የሚሠጥ መሆኑም ተገልጧል፡፡
Hey There. I found your blog using msn. This is a really well
written article. I’ll make sure to bookmark it and come back to read more of your useful information. Thanks for the post.
I’ll definitely return.