ሥራ አመራር ኢንስቲትዩቱ የ2015 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ አመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱን ገምግሟል

ኢንስቲትዩቱ የ2015 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ አካሄዷል፡፡ የኢንስቲትዩቱ የዕቅድ፤በጀትና ፕሮጀክት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ተወካይ ዳይሬክተር አቶ ተስፋየ ኃ/ስላሴ በሩብ አመቱ በእቅድ ከተቀመጡ ከተግባራት ዉስጥ በ2015 በጀት ዓመት የተሻለ አፈፃፀም ማስመዘገቡን መቻሉን ባቀረቡት ሪፖርት አስታዉቀዋል፡፡

በሪፖርቱ በመጀመሪያ ሩብ አመት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በተሳካ ሁኔታ መተግበራቸዉና ለፈጻሚና ለአጋር አካላት በማስተዋወቅ የታቀዱ ተግባራት በእቅዱ መሰረት መፈማቸዉን፤ኢንስቲትዩቱን በስፋት ለማስተዋወቅ የገጽታ ግንባታና የፕሮሞሽን ስራዎች መተግበራቸዉ፤የጥምር ጦር አባላት ድጋፍ ስራችን የታየዉ መነሳሳት፤የፋሲሊቲ አገልግሎት ስራዎች፤የተጠናከረ የአቅም ግንባታ ስራዎች፤የሰራተኛዉ የስራ ዲሲፒሊን ቁርጠኝነት አገልግሎት አሰጣጥና መልካም ግንኙነት በጥንካሬ ጠቅሰዋል፡፡

የመፈፀም አቅምን የሚያሳድጉ የአቅም ግንባታ ስራዎች፤አጫጭር ስልጠናዎች፤ችግር ፈችና ሀብት አመንጭ የምርምር ስራዎች፤የተቋሙ የዉስጥና የዉጭ ስትራቴጅክ አጋርነት ስራዎች፤የአሰራርና አደረጃጀት ስራዎች፤ከይዘናዊ የስራ ባህል ግንባታ ስራዎች፤የመደበኛ የመማር ማስተማር ስራዎች መጠናከር የሚገባቸዉ ተግባራት እንደሆኑ ተጠቅሰዋል፡፡ በግምገማዉ በቀረበዉ ሪፖርት መሻሻልና መጠናከር የሚገባቸዉ ጥያቄዎችና ገንቢ አስተያየቶች በሰራተኞች ተነስተው በኢንስቲትዩቱ የበላይ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን በሩብ አመቱ ስኬታማ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በመፈፀም ከባለፈዉ ሩብ አመት ሲነጻጻር የተሻለ አፈፃፀም የፈፀምንበትና ለቀጣይ አቅም ሊሆን የሚችል ቁመና ላይ የምንገኝ ሲሆን ሁሉም ሰራተኛ ለተሰጠ ተልዕኮ ዉጤታማነት በጋራና በቅንጅት ተግቶ መስራት እንዳለበት ተመላክቷል፡፡ በመጨረሻም የሰራተኛ ሸማቾች ማህበር መመስረቻ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ የማህበሩን የአደረጃጀትና የአሰራር አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡