የአብክመ አመራር አካዳሚ በክልሉ ም/ቤት በአዋጅ ቁጥር 221/2007 መሰረት ከፍተኛ የትምህርት፤የስልጠናና የምርምር ተቋም ሆኖ ተቋቋመ፡፡

እንደገናም በአዋጅ ቁጥር 280/214 ተግባርና ሀላፊነቱን ሳይቀይር በስራ ላይ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡በዚህም መሰረት የክልሉ መንግስት በአዋጅ በተሰጠው ፈቃድ መሰረት ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ያስመረቀ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁንና አዲሱ የከፍተኛ ትምህርት ስልጠና አዋጅ የመንግስት የትምህርት ተቋማትንም ጨምሮ ፈቃድ የማግኘት ግዴታ ያለባቸው መሆኑን ስለሚደነግግ ይህንን ተከትለን ለባለስልጣኑ ያቀረብነው ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ የኢፌድሪ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የከፍተኛ ትምህርት ፕሮግራም ስልጠና ለማካሔድ ፈቃድ የሰጠን በመሆኑ መላው የአካዳሚያችን ማህበረሰብ ከፍተኛ ደስታ የተሰማን መሆኑን እየገለፅንየክልላችን ህዝብና መንግስት አካዳሚው የከፍተኛ ትምህርት፤ የአጫጭር ስልጠናዎች እና የችግር ፈች ምርምር ተቋም እንዲሆን የሰጠውን ሀላፊነት በልበ ሙሉነት እና በትጋት እንዲፈፅም ትልቅ መደላድል መሆኑን ስንገልጽ በደስታ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *