የአብክመ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ለአብክመ አካባቢ ጥበቃ ቢሮ የማኔጅመንት አባላት ለተከታታይ አራት ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

መጋቢት 20/2016 ዓ.ም የዚህ ስልጠና አስፈላጊነት እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ፤ፍትሀዊ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እና የሚያጋጥሙ ችግሮችን በጊዜና በአሰራር በመፍታት ቢሮው ራዕዩን ለማሰካት የአመራሩን የመምራት የመደገፍና የመወሰን አቅሙን ለማዳበር ይረዳ ዘንድ በማሰብ Decision making and problem solvingእና Team building በሚሉ ርዕሶች ዙሪያ በአብክመ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት አማካሪዎችና መምህራን ስልጠናው ተሰጥቷል፡፡ በስልጠናውም የአብክመ አካባቢ ጥበቃ ቢሮ 14 የማኔጅመንት አባላት ተሳትፈዋል፡፡