የአብክመ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ለሰራተኞቹ በጊዜአዊነት ለልማት አገልግሎት የሚውል መሬት ሰጠ፡፡

ኢንስቲትዩቱ የሰራተኞቹን የኑሮ ውድነት ለመደጎም በሚል መነሻ ፍላጎት ላላቸው 19 ሰራተኞች በቅጥር ግቢው ውስጥ ከሚገኘው መሬት ለተለያዩ ተክሎች ልማት እንዲውል በማለት ካለፈው ሰኔ 2016 በጀት ዓመት ጀምሮ በጊዜአዊነት ሰጥቷል፡፡

የአረንጓዴ አሻራ ተምሳሌት በሆነው የአብክመ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት በጊዜአዊነት የልማት መሬት የወሰዱ ሰራተኞች በዋናነት በቆሎ፤ ነጭ ሽንኩርት፤ ቃሪያ፤ ጎመን፤ አተርና ሌሎችን አትክልቶችን በማልማት የደረሱትን ለሽያጭና ለምግብነት እያዋሉ እደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *