የአብክመ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት በባህር ዳር ከተማ ለሚገኙ 2 ትምህርትቤቶች የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ
መስከረም 04/01/2017 ዓ.ም የአብክመ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት የክልሉ ከፍተኛ የትምህርትና የስልጠና፣ የምርምር፣ የምክር አገልግሎት ሰጭ ተቋም ከመሆኑም በላይ የማህበረስብ አገልግሎት የመስጠት ሀላፊነት ያለበት መሆኑ ይታወቃል ።በዚህም መሠረት በባህር ዳር ከተማ ለሚገኙ ሁለት ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ለችግር የተጋለጡ 100 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
በድጋፉ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሰብስበው አጥቃው እንደገለፁት ዛሬ የሰጠነው የቁሳቁስ ድጋፍ ለ2 ትምህርት ቤቶች 1ኛ ደረጃ የፈለገ አባይ እና እውቀት ፋና ትምህርት ቤቶች በ2017 ዓ.ም ትምህርታቸውን ለመቀጠል የተቸገሩ ተማሪዎችን ለመደገፍና የመተጋገዝ፣ የመረዳዳት፣ ፍቅርን የመግለፅ የወንድማማችነትና አንድነትን ለማጥበቅ የተወሠደ ጅምር ሥራ ነው በቀጣይም ኢንስቲትዩታችን ይህንን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልፀዋል፡፡
በዕለቱ የተገኙት የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ምክትል መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ትበይን ባንቲሁን እንደገለፁት ተማሪዎችን በአግባቡ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የማድረግ ኃላፊነት የመምህራንና የወላጆች መሆኑንና እንዲሁም ወላጆች ልጆቻችሁን በአግባቡ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የማድረግ ኃላፊነት አለባችሁ ብለዋል፡፡
ድጋፍም በኢንስቲትዩቱ ም/ ፕሬዚዳንት በዶ/ር ሰብስበው አጥቃው ፣በኢንስቲትዩቱ በህዝብ ግንኙነት ኃላፊ በአቶ ጋሻው ገብሬ፣ በባህር ዳር ከተማ መምሪያ ኃላፊ በወ/ሮ ተበይን ባንቲሁን100 /መቶ/ ለሚሆኑ ተማሪዎች እስክርቪቶና ደብተር ተበርክቷል፡፡
ለድጋፍ 72,000, (ሰባ ሁለት ሺህ ብር ) ወጭ ተደርጓል፡፡
![](https://ala.edu.et/wp-content/uploads/2021/03/IMG_5124-min-1024x431.jpg)