የአብከመ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት በሁለተኛ እና ሦስተኛ ዲግሪ መርሐ ግብር ያሰለጠናቸውን ከ200 በላይ ተማሪዎች እያስመረቀ ነው።
ከተመራቂዎች መካከል በኢንስቲትዩቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሦስተኛ ዲግሪ ተመራቂ ይገኝበታል።
የአማራ ክልል ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት በሁለተኛ እና በሥስተኛ ዲግሪ መርሐ ግብር ያሰለጠናቸውን 222 ተማሪዎችን አስመረቀ። ከተመራቂዎቹ መካከል 58ቱ ሴቶች ሲኾኑ አንድ ተመራቂ ደግሞ የሦስተኛ ዲግሪ ሰልጣኝ ነው።
ተመራቂዎቹ በፒስ ኤንድ ዴቨሎፕመንት፣ በፕሮጀክት ማኔጅመንት፣ በፐብሊክ ፖሊሲ እና አመራር እንዲሁም በፖለቲካል ኢኮኖሚ የትምህርት ዘርፎች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ናቸው።
በምረቃ መርሐ ግብሩ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣ የተመራቂ ቤተሰቦች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።