የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ሁሉም ሰራተኞች በተገኙበት የ2016 በጅት አመት የዘጠኝ ወራት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ

ክትትል እና ግምገማ አዳዲስ አስተሳሰቦችን እና የመረጃ አሰባሰብ ዘዴዎችን ለማዳበር የሚረዳን ከመሆኑም በላይ ተቋማችን ያለበትን የግብ ስኬት ደረጃ ለመረዳት አስፈላጊ መሳሪያ ነው። በዚህ ሂደት መረጃዎችን ለመሰብስብ፣ለመርመር እና ትክክለኛ ውሳኔ በማስተላለፍ ግቦቻችን እንዲሟሉ ይረዳናል።የመስሪያ ቤትን እቅድ መሳሪያ አበጅትህ ተከታተለን ካለካን ውጤታማነት ይርቀናል። ምክኒያቱም የተሰጠን ጊዜ አጭር ስለሆነ ጊዜን በስስት አይተን ወደ ውጤት ካልቀየርን ስኬታማ ልንሆን አንችልም። በሌላ መንገድ መለካት ካቃተን ማሻሻል አንችልም። ክትትል እና ግምገማ የየትኛውም የተደራጀ መዋቅር የስራ ውጤታማነት የምንለካበት ሁነኛ መሳሪያ በመሆኑ።

የክትትልና ግምገማ አላማ የባለድርሻ አካላት ስለ መስሪያ ቤታችን ያላቸውን ግንዛቤ ለመገምገም፣አሳታፊ የግምገማና ክትትል ባህልን ለማጎልበት፣በመስሪያ ቤቱ ሊገጥሙ የሚችሉ አደጋወችን መቀነስ እንድንችል፣ስልታዊ እና ሙያዊ አስተዳደርን ለማሳደግ፣ የአፈጻጸም ሂደትን ውጤታማነት እና ችግሮችን በመገምገም ማረም እንድንችል ያግዘናል፡፡የክትትልና ግምገማ አላማ በፕሮግራም አተገባበር ላይ መደበኛ እና ወቅታዊ ግብረ መልስ ለመስጠት፣መሻሻል የሚገባቸውን ተግባራትን ለመለየት እና የታሰበው ውጤት እንዲመጣ ማስተካከያ ማድረግ እንድንችል የሚያደርገን ሁነኛ መሳሪያ ነው።

ሁልጊዜም በዳይሬክተር፣በዘርፍ፣በጠቅላላ ሰራተኛ መድረክ በየሩብ አመቱና አስፈላጊ ሲሆን ደግሞ ከዚህም ባነሰ ጊዜ የክትትልና ግምገማ መድረክ በመፍጠር ከእቅዳችን አንጻር ያለንበትን ሁኔታ የመገምገም ባህል ያለው የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት የተቋሙ ሁሉም ሰራተኞች በተገኙበት የ2016 በጅት አመት የዘጠኝ ወራት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተከናውኗል፡፡ የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱ በመ/ቤቱ የዕቅድና በጀት ክትትል ባለሙያ በአቶ ተስፋዩ ኃ/ስላሴ ቀርቧል፡፡ በሪፖርቱ ላይ ሰራተኞች ጥያቄዎችና አስተያየቶችን የሰጡ ሶሆን በመጨረሻም የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮችና የሚመለከታቸዉ ዳይሬክተሮች ለተነሱ ሀሳቦችና ጥያቄዎች ምላሸ ተሰጥቷል፡፡

መድረኩ የተመራዉና የማጠቃለያ የስራ መመሪያ የተሰጠዉ በተቋማችን ፕሬዝዳንት አቶ እሱባለዉ መሠለ ሲሆን በየደረጃዉ የጀመርናቸዉን የድጋፍና ክትትል ስራዎች አጠናክረን እንድንቀጥልና ከግማሽ ፐርሰንት በታች ያሉ አፈጻፀሞችን ለይተን የማሻሻያ ስራ ልንሰራ ይገባል ብለዋል፡፡

1
4