የአመራር አካዳሚ ተማሪወችን አስመረቀ

06/06/2013 ዓ.ም የአማራ አመራር አካዳሚ በህዝብ አመራርነት እና በፖለቲካል ኢኮኖሚ በመደበኛ መርሃ-ግብር ያስተምራቸውን 37 የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ዛሬ አስመረቀ ።አካዳሚው የክልሉ መንግስት ዩኒቨርሲቲ ከሆነ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በተጠቀሱ የትምህርት መስኮች በሁለተኛ ሲያስመርቅ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ።በአሁኑ ወቅት አካዳሚው 103 ተማሪዎችን በአራት የትምህርት ዘርፎች በሁለተኛና በሶስተኛ ዲግሪ በማሰልጠን ላይ መሆኑን የአካዳሚው ፕሬዝዳንት ዶክተር ማተቤ ታፈረ በምረቃው ወቅት ገልጠዋል ።በቀጣይም በእንድ የ2ኛ እና በአንድ ተጨማሪ የትምህርት ዓይነት የማስተርስና ዶክትሬት ፕሮግራም ለመጀመር ዝግጅት ላይ መሆኑን ጠቅሰዋል ።የክልሉ መንግስትና ባለድርሻ አካላትም እስካሁን ለአካዳሚው አዚህ ደረጃ መድረስ ያደረጉትን ደጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል ።ኢትዮጵያና አማራ በህግ ማስከበሩ ዘመቻ ለብልፅግናቸው መሰረት የሆነ ድል መቀዳጀታቸው የሚያኮራ ቢሆንም አሁንም ቢሆን ፈተናዎች አሉባቸው ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር እና የዕለቱ የክብር እንግዳ የተከበሩ አቶ አገኘሁ ተሻገር ገልጠዋል ።ይህን ችግር መሻገር የሚቻለውም ወቅቱ የሚጠይቀው በዕውቀትና ጥበብ የሚያሻግር አመራር ሲኖር መሆኑን ተናግረዋል ።ከዚህ አኳያ ቀጣዩን ምርጫ ጨምሮ ተመራቂዎቹ የአመራር ብቃት እና ቁርጠኝነትን ተላብሰው የሚሰጣቸውን ስምሪት በአግባቡ ለመወጣት መዘጋጀት እንዳለባቸው አሳስበዋል።ወቅቱ ከምንግዜውም በላይ የአመራር ብቃት እና ቁርጠኝነት የሚጠይቅ መሆኑን መገንዘብ እንዳለባቸውም ፕሬዝዳንቱ አሳስበዋል፡፡ ተመራቂዎቹ ከዚህ በፊት ያካበቱትን የአመራር ልምድ እና በአካዳሚው ቆይታቸው በጥብቅ ዲሲፕሊን የቀሰሙትን የዕእውቀት፣ የክህሎት እና የአመለካከት ከፍታ በመጠቀም ለተሻለ ተልዕኮ እና ውጤታማነት ዝግጁ መሆን እንዳለባቸው ደግሞ የክልሉ ም/ቤት አፈ-ጉባዓ ክብርት ወርቅሰሙ ማሞ ጠይቀዋል ።በትናንሽ ስኬቶች ሳይረኩና በሚያጋጥማቸው ፈተናዎች መሸበር እንደሌለባቸው እና ለበለጠ ስኬት እንዲተጉ ደግሞ የአካዳሚው የቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ይልቃል ከፋለ መክረዋል ።የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ፈንታ ማንደፍሮ ለተመራቂዎቹ ዲግሪ ሰጥተዋል ።አራት ነጥብ ያመጡ ሁለት ወንዶችና 3 ነጥብ 91 ያመጣችው አንዲት ሴት ተመራቂ ከዕለቱ የክብር እንግዶች የወርቅ ሜዳልያና ልዩ ሽልማት ተቀብለዋል ።ተማሪዎቹ በቆይታቸው የቀለም ትምህርት ብቻ ሳይሆን የሀገር ፍቅር፣ የህህዝብ አገልጋይነትን፣ በራስ መተማመንን እና መልካም ስብዕናንም መቅሰማቸውንና ይህንንም በተግባር ለመተርጎም ዝግጁ መሆናቸውን ገልጠዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *