የአብክመ ሳይንስ ቴክኖሎጅና ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ሰራተኞች እና አመራሮች የስራ ላይ ስነ-ምግባር ስልጠና ወሰዱ
የአብክመ አመራር አካዳሚ ለአብክመ ሳይንስ ቴክኖሎጅና ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ሰራተኞች እና አመራሮች የስራ ላይ ስነ-ምግባር
ላይ
ያተኮረ ስልጠና ከየካቲት 10/2013 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት በመስጠት ተጠናቋል፡፡
የሥልጠናው ዓላማ የአመራሮችንና ከፍተኛ ባለሙያዎችን እውቀት ፣ ክህሎት ፣ተቋማዊ የሥራ ሥነ ምግባር፣ አመለካከትና ተነሳሽነትን ማሳደግ ነው ሲሉ የአካዳሚው አማካሪ አቶ ጊዜው ታደሰ እና አቶ ታምሩ ተመስገን ገልፀዋል፡፡ አማካሪዎች አክልውም ስልጠናው የሥነ-ምግባር ዓይነቶችን በመለየት እና በድርጅት ውስጥ የስነ-ምግባር ባህሪያትን በማሳወቅ የሰራተኞችን እውቀት አመለካከትና ክህሎት በመቀየር እና ጠንካራ ሰራተኛ እንዴት ማበረታታት እንደሚቻል ለማሳየት ነው ፡፡
ይህ ስልጠና በዚህ ወቅት አስፈላጊና ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ በመሆኑ ሁሉም የክልል መ/ቤቶችና ድርጅቶች ሊሳተፉ የሚገባ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የስልጠና ተሳታፊዎችም በዚህ ስልጠና መሳተፋችን በስራ ቦታችን ምን አይነት ስነ-ምግባር በመያዝ ስኬትን ማምጣት እንደሚቻል የሚያመላክት ነው በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ በስልጠናውም 44 የሳይንስ ቴክኖሎጅና ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽንአመራሮችናሰራተኞች የስልጠናው ተሳታፊ መሆናቸው ታውቋል፡፡