የማህበረሰብ አገልግሎት ድጋፍ ዓላማ የመተጋገዝ፣ ፍቅርን የመግለፅ እና ወንድማማችነትን ለማጥበቅ መሆኑ ተገለፀ

ማህበረሰባዊ ሃላፊነታችን የሚለካው ለሰራተኞቻችን እና ለአካባቢው ማህበረሰብ ኑሮ መሻሻል ባበረከትነው አስተዋጽኦ ልክ ሲሆን ይህ ደግሞ ፍቅርን ይስባል ፍቅር ደግሞ ለሌሎች መስዋዕትነት የምንከፍልበት የጋራ መለያችን መሆኑ የታወቀ ነው። የሰዎችን ጉድለት ለመሙላት በድርጊት ስንነሳ ፍቅርን የመግለጽ ዕድላችን እየጨመረ ይሄዳል። የህዝብን ልብ ፣ አእምሮ እና ነፍስ በመያዝ ቅቡልነትን የምናተርፈው ጉድለቱን በመሙላት ነው ፡፡

 የሰው ልጅ የመኖሩ ትልቁ አላማ ደግሞ ለራሱ በልቶ ለማደር ብቻ ሳይሆን ለችግረኛ ወገኞቹ ደራሽ ለመሆን ነው።ይህንን መሠረት ያደረገው ተቋማችን ዛሬ ሚያዚያ 24/2016 ዓ.ም የወር ደሞዛቸው አነስተኛ ለሆኑ 58 ለተቋማችን ሠራተኞች እና በባህር ዳር ከተማ የጊዮን 2ተኛ ደረጃ መሰናዶ ት/ቤት 15 የማህበረሰብ ክፍሎች በአጠቃላይ ለ73 እህትና ወንድሞቻችን የፋሲካ በዓል መዋያ የሚሆን የዘይት፣ የፊኖ ዱቄት እና የዶሮ ድጋፍ ተደርጐላቸዋል፡፡

ድጋፉን የተቋማችን ፕሬዚዳንት አቶ እሱባለው መሠለ የሰጡ ሲሆን በዚሁ ዕለት ዛሬ የሰጠነው የበአል መዋያ ድጋፍ የቁሳቁስ ድጋፍ ብቻ ሣይሆን የመተጋገዝ፣ የመረዳዳት፣ ፍቅርን የመግለፅ የወንድማማችነት እና አንድነትን ለማጥበቅ የተወሠደ ጅምር ሥራ መሆኑን ሊታወቅ ይገባል ያሉ ሲሆን አክለውም በዚህ ሁኔታ ማህበረሰባዊ ኃላፊነታችን ለመወጣት በትንሹ ጉዞ ጀምረናል አቅማችን እየጐለበተ ሲሄድ ደግሞ አገልግሎታችን ከፍ ባለ ተደራሽነት አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡ ለድጋፍ 117,106.80 (አንድ መቶ አሥራ ሰባት ሺህ አንድ መቶ ስድስት ብር ከሰማንያ ሳንቲም) ወጭ ተደርጓል፡፡

1
2
3