የመማር ማስተማር ስራዉ ዉጤታማና የተሻለ መሆኑን ተመራቂ ተማሪዎች ገለፁ

ቀን 08/07/2014ዓ.ም

የአብክመ አመራርአካዳሚ የ2014 ዓ.ም የድህረ-ምርቃን ተማሪዎች የማማርማስተማር ስራዉ ዉጤታማና የተሻለ መሆኑን ገለፁ፡፡

አካዳሚዉ በማማርማስተማር ስራዎችና የአሰራር ስርዓት እና የተጀመረዉን ዉጤታማ የመመማርማስተማር ሂደት አጠናክሮ ለማስቀጠል ያለመ ዉይይት ከዕጩ ምርቃን ጋር የዉይይት መድረክ አካሂደዋል፡፡ በዉይይቱም በአካዳሚዉ ግቢ ዉስጥ የሚሠጠዉ የመማርማስተማር ስራምቹ የግቢዉ በየቴክኖሎጅ አቅርቦት በመጠቀም የተማሪዎችን አቅም ክህሎት እዉቀት የሚያሳድግ መሆኑን ተገልጿል፡፡ ዕጩ ምርቃን ተማሪዎች በመድረኩ አካዳሚዉ ወደ ስቴት ዩኒቨርስቲ የሚያደርገዉን ሽግግር ትኩረት ሠጥቶ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

በዉይይቱም በመማርማስተማር አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ እና የሚያጋጥሙ አስተዳደራዊ የፋስሊቲ ችግሮች ጥያቄዎች ተነስተዉ በአካዳሚዉ የትምህርት ናስልጠና ዘርፍ ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሰብስበዉ አጥቃዉ እና የአካዳሚው የበላይ አመራሮች ማብራሪያና ምላሽ ተሠጥቶበታል፡፡ አመራር አካዳሚዉ በአራት የትምህርት ፕሮግራሞች ከ80 በላይ ያሠለጠናቸዉን ዕጩ ምርቃን ለሁለተኛ ጊዜ ያስመርቃል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *