ታላቁ የአባይ ድልድይ ለተሻለ ነገ የተስፋ ምልክት ነው፡፡

የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ለኢኮኖሚ እድገት እና አገራዊ ልማት አንቀሳቃሽ መሆኑ የታወቀ ነው። ታላቁ የአባይ ድልድይ የትብብር አስፈላጊነት መስታውት፤የሜጋ ፕሮጀክቶች ፈተናዎችን በጽናት የመፍታት ባህል ግንባታ ተመክሮ፣የኢኖቬሽን እና የቴክኖሎጂ እድገት ሃይል ማሳያ፣ በህብረተሰቡ ልማት ላይ የምህንድስና ጥቅም ትኩረት አድርገን እንድንሰራ የሚያነሳሳን እና ሰወች ለህዝብ ጥቅም ሲሉ የከፈሉትን መስዋዕትነት እንዳንዘነጋ የሚያደርገን ውብና ማራኪ ታላቅ ድልድይ ነው፡፡

ታላቁ የአባይ ድልድይ በአካባቢው ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴን ያነሳሳል፡፡ በማህበረሰብ መካከል ግንኙነትን ይፈጥራል፡፡ ከዚህም ሌላ የሸቀጦች እና የሰዎች እንቅስቃሴን የተመቻቻ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ ይህም የንግድ እና የኢንቨስትመንት መጨመር ያስከትላል፡፡ በተጨማሪም የድልድዮ ግንባታ የስራ እድልንም የሚፈጥር ይሆናል፡፡

ታላቁ የአባይ ድልድይ ለተሻለ ነገ የተስፋ ምልክት ነው፡፡ ድልድያችን በጋራ የልማትና እድገት ምናባችን ውስጥ ያለውን ፋይዳ እና ጥቅም እጅግ ግዙፍ ነው። ድልድዮ ሁለት የተለያዩ ቦታወችን እንደልብ ከማገናኘት ባሻገር፣ ብዙ ተስፋን፣ እድገትን እና አንድነታችን የሚያጠናክር ምልክታችን ነው። አዳዲስ እድሎችን እና ግንኙነቶችን የሚያነቃም ነው ብለን እናምናለን፡፡የእድገታችን እና የለውጥ እምቅ አቅማችን ማሳያም ሆኖ የሚያገለግል ነው፡፡ ታላቁ የአባይ ድልድይ በታላቅነቱ እና በምህንድስና ድንቅነቱ የማህበረሰቡን ምኞቶች እና ህልም የሚያሳድግ ይሆናል፡፡ ታላቁ የአባይ ድልድያችን የትኛውንም አይነት ተግዳሮቶች ቢያጋጥመንም ሁልጊዜም ብሩህ ተስፋ በፊታችን እንዳለ አመላካች የብርሃን ፍንጣቂያችን ነው ፡፡