በአብክመ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት የምርምር ፎረም ተካሔደ
መስከረም 08/2017 ዓ.ም የአብክመ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ለ14ኛ ዙር የጥናትና ምርምር ፎረም አካሄዷል፡፡
በምርምር ፎረሙ የኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ ተመራማሪ አቶ አሳቤ ምህረቴ “An Assessment of the Attributes of Good Leadership Practices of Middle Level Leaders in Government Organization (in the case of selected Bureaus of ANRS” በሚል ርእስ የጥናትና የምርምር ስራቸዉን አቅርበዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ የምርምርና ሥርፀት ዘርፍ ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ቹቹ አለባቸው የምርምር ፎረሙን ሲከፍቱ የአብክመ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት በአዋጅ ሲቋቋም የተሰጡት ተልዕኮዎች የፐብሊክ ሴክተሩን በትምህርት፤ በአጭር ጊዜና በረዥመም ጊዜ ስልጠና፤ በምርምርና ማማከር አቅም ለመገንባት ነው፡፡
ስለሆነም ለክልላችን ልማትና እድገት ይረዳ ዘንድ የምርምር ስራዎችን በማጠናከር መጠቀም እንዲሁም ባለድርሻ አካላትን ማሳተፍና ማሳደግ አለብን ብለዋል፡፡ የኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምር ስራዎች ከፍ እንዲሉ የጥናትና ምርምር አዉደ ጥናቶች በዘላቂነት ተጠናክረዉ ሊቀጥሉ እንደሚገባ በመጠቆም ፎረሙን ከፍተዋል፡፡
በእለቱ ተሳታፊ የነበሩ ከአስራ ሁለት ሴክትር መስሪያ ቤቶች ከፍተኛ አመራሮች የክፍል ሀላፊዎችና፤የኢንስቲትዩቱ አመራሮችና ሰራተኞችም በቀረበው የጥናት ጹሁፍ አስተያየቶችና ጥያቄዎችን በማንሳት ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡
የፎረሙ አመቻች የሆኑት የኢንስቲትዩቱ መምህር ዶ/ር ብነግረው ዋሌ በበኩላቸው ፎረሙን በመሩበት ወቅት የጋራ የሆነ ክልላዊ ችግር ነው ያለን፡፡ ስለሆነም ዛሬ በዚህ ፎረም የተገኛችሁም ሆነ ሌሎች ተቋማት ችግሮቻችንን ለመፍታት አማራጩ ሪሰርቾችን መስራትና መጠቀም በመሆኑ ከአብክም ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ጋር እየተናበብንና ተቀናጅተን በመስራት ችግሮቻችን ልንቀርፍ ይገባል በማለት አሳስበዋል፡፡
በመጨረሻም የአብክመ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ም/ፕሬዘዳንት ዶ/ር ሰብስበው አጥቃው ፎረሙን ሲያጠቃልሉ የአብክመ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት የክልሉ የእውቀት ማበልፀጊያ ተቋም እንዲሆን ታስቦ የተቋቋመ ተቋም ነው፡፡ በመሆኑም ሴክትር መስሪያቤቶች በትምህርት፤በስልጠና በምርምርና በማማከር በቀጣይ በተጠናከረ መልኩ አብረን መስራት አለብን በማለት እና ከተሳታፊዎች ለተነሱ ሀሳቦች ማብራሪያ በመስጠት አቅራቢዎችንና ተሳታፊዎችን በማመስገን ፎረሙን አጠቃለዋል፡፡