በአብክመ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት የምርምር ፎረም ተካሄደ

ሚያዚያ 11/2016 ዓ.ም የአብክመ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ለ11ኛ ዙር ሁለት የጥናትና ምርምር ስራዎችን ፎረም አካሄዷል፡፡ የምርምር ፎረሙ የኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ ተመራማሪ አቶ አሳቤ ምህረቴ “An Assessment of the Attributes of Good Leadership Practices of Middle Level Managers in Government Organization, the case of ANRS at Bureau Level” በሚል ጥናት እንዲሁም በኢንስቲትዩቱ የምርምርና ልማት ዳይሬክተር አቶ ዉብሽት አለኸኝ The Assessment of Organizational Gaps in ANRS Management institute” በሚል ርእስ ሁለት የጥናትና የምርምር ስራዎቻቸዉን አቅርበዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ የምርምርና ሥርፀት ዘርፍ ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ቹቹ አለባቸው የምርምር ፎረሙን ሲከፍቱ የአብክመ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት በአዋጅ ከተሰጡት ተልዕኮዎች አንዱ ችግር ፈች ምርምሮችን ማድረግና ሲፖዚየሞችን ማካሄድ ነው፡፡ ስለሆነም ለክልላችን ልማትና እድገት የምርምር ፎረምን ለማሳደግ የምርምር ስራዎችን በማጠናከር መጠቀም እንዲሁም ባለድርሻ አካላትን ማሳተፍና ማሳደግ አለብን ብለዉ፤ ኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምር ስራዎች ከፍ እንዲሉ የጥናትና ምርምር አዉደ ጥናቶች በዘላቂነት ተጠናክረዉ ሊቀጥሉ እንደሚገባ በመጠቆም ፎረሙን ከፍተዋል፡፡በእለቱ ተሳታፊ የነበሩ ከአብክመ ሲቪል ሰርቪሽ ኮሚሽን፤ከባህር ዳር የኢንስቲትዩቱ መደበኛ ተማሪዎች መምህራን፤የኢንስቲትዩቱ አመራሮችና ሰራተኞችም በቀረበው የጥናት ጹሁፍ አስተያየቶችና ጥያቄዎችን በማንሳት ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በመጨረሻም የአብክመ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት የምርምርና ስርፀት ዘርፍ ም/ፕሬዘዳንት ዶ/ር ቹቹ አለባቸው ፎረሙን ሲያጠቃልሉ ለሀገራችን ብሎም ለክልላችን ልማትና እድገት እንደዚህ አይነት የምርምር ስራዎችን በማጠናከር መጠቀም እንዲሁም ባለድርሻ አካላትን ማሳተፍና ማሳደግ አለብን ሲሉ ገልጸዋል፡፡

1
3

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *