መሪ ውጤታማ ድርድር በማድረግ ብቃቱ ይለካል ለዚህ የሚጠቅሙ ቁልፍ መርሆዎች፡-

  • ለድርድር በቂ ዝግጅት ማድረጉን ደጋግሞ ማረጋገጥ፤
  • ብቃት ያለው ተግባቦት እና መተማመንን የሚፈጥር አቅም ያለው መሆኑን መረዳት፤
  • በያዘው የአላማ ፍላጎት ላይ ያተኩሩ የድርድር ሀሳቦችን በቅደም ተከተል እማራጮችን ለይቶ ማስቀመጡን ማረጋገጥ፤
  • በቅደም ተከተል የተያዙት የመደራደሪያ ሀሣቦች ሁሉ ተቀባይነት ሊያገኙም ላያገኙም እንደሚችሉ በመረዳት ተለዋዋጭ የሃሳብ አማራጮችን መያዝ፤
  • በመርህ ደረጃ የተያዙ የመደራደሪያ ሀሳቦችን በተደራጀ መንገድ የመግለጽ አቅም መኖርን ማረጋገጥ፤
  • የማዳመጥ እና የማመዛዘን ችሎታ መኖርን ማወቅ፤
  • የመደራደር በቂ ልምድ፣ እውቀት፣ ችሎታ እና ለያዘው አጀንዳ ታማኝነት ያለው መሆንን መረዳት።
ለድርድር አስፈላጊ የሆኑ የቅድመ ዝግጅት ሁኔታዎች ምንድን ናቸው?
  • የዝግጅት እና የዕቅድ ክህሎት መኖር፤
  • ስለ ድርድር ርዕሰ ጉዳዩ በቂ እውቀት የመኖር፤
  • ግፊት እና ጥርጣሬ በበዛበት ሁኔታ ውስጥ በግልፅነት እና በፍጥነት የማሰብ ችሎታ መኖር።

በድርድር ሂደት ውስጥ ግጭት ጥሩ ነው ። ምክንያቱም የሁለት ሃሳቦች ፍጥጫ ለመረዳት ጠቃሚ ከመሆኑም በላይ ድርድሩ በውጤታማነት ሲጠናቀቅ ሁሉም የሚተማመኑበት ሶስተኛ ስላማዊ መንገድ የሚፈጥር በመሆኑ ነው።

                        ሉክ ሮበርትስ