ለአብክመ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ሰራተኞች ስለ ስኳር ህመም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ!

መስከረም 21/2017 ዓ.ም ለአብክመ ስራ አመራር ኢንስቲትዪት ለሠራተኞች ስለስኳር ህመም፤መከላከል ምልክቶችና መንስኤዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡

የአብክመ ጤና ቢሮ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ግርማ ደርሶ ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች ውስጥ ስለ ስኳር ህመም ምንነት፤መከላከል፤ መንስኤዎች፤ የስኳር ህመምን ለመከላከል የሚጠቅሙ የአመጋገብ ስርአቶች፤ቅድመ ምርመራና የስኳር ህመም የሚያስከትላቸውን ውስብስብ የጤና ችግሮች ያካተተ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ተሰጥቷል፡፡

በቀረቡት የመወያያ ርዕሶች ላይም በተሳታፊዎች ጥያቄዎች እና አስተያየቶችን በማንሳት ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በመጨረሻም ከባህዳ ዳር ጤና ጣቢያ በመጡ የጤና ባለሙያዎች የስልጠናው ተሳታፊዎች የግፊት እና የስኳር መጠን ልኬት አገልግሎት በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *